ግልጽ ዋጋ
ስንት እንደሚያስከፍል ከመምጣትዎ በፊት ይወቁ
እነዚህ ዋጋዎች የምርመራውን፣ የማደንዘዣውን እና የመጀመሪያውን ክትትል ያካትታሉ። ተጨማሪ ሥራ ካስፈለገ በጽሑፍ ተሰጥቶዎት ይፈቀዳል።
የክፍያ ዕቅድ ይመልከቱየክፍያ አማራጮች
ትልቅ ሥራ በአንድ ጊዜ መክፈል የለብዎትም
በቀጠሮ ይክፈሉ
በጥያቄ
ለምርመራ፣ ለንጽሕና እና ለመሙላት
- ከሥራው በኋላ ይከፍላሉ
- ደረሰኝ በተመሳሳይ ቀን
- የቅድሚያ ክፍያ የለም
የሦስት ወር ክፍያ
በጥያቄ
ከ5,000 ብር በላይ ለሆኑ ሥራዎች — ዘውድ፣ ሥር ቦይ እና ጥርስ ማሠሪያ
- ሢሶ ሲጀመር፣ ሢሶ በመሐል፣ ሢሶ ሲያልቅ
- ወለድ እና የአገልግሎት ክፍያ የለም
- የመታወቂያ ቅጂ ብቻ ይጠየቃል
የብሬስ ወርሃዊ ክፍያ
1800 ብርበወር
የመጀመሪያ ክፍያ 8,000 ብር ከዚያ ወርሃዊ
- ወርሃዊ ማስተካከያ ተካትቷል
- የተሰበረ ብራኬት በነጻ ይተካል
- የመጨረሻው ሪቴነር ተካትቷል
በኢንሹራንስ
በጥያቄ
- ናይል፣ ኒያላ እና አዋሽ ኢንሹራንስ
- ካርድዎን እና መታወቂያዎን ይዘው ይምጡ
- የተቀነሰውን ብቻ ይከፍላሉ
ክፍያ በጥሬ ገንዘብ፣ በቴሌብር፣ በካርድ ወይም በባንክ ዝውውር። ወለድ አንጨምርም።
ሰዎች ከመምጣታቸው በፊት የሚጠይቁት
ያማል?
መርፌው ከመግባቱ በፊት ድዱ ላይ የሚቀባ ማደንዘዣ ጄል እንጠቀማለን፤ ስለዚህ መርፌውን አይሰማዎትም። በሥራው መሐል ማንኛውም ጊዜ እጅዎን ካነሱ እናቆማለን።
የተነገረኝ ዋጋ ይለወጣል?
የተጻፈልዎት ዋጋ ይጸናል። በሥራው መሐል ተጨማሪ ችግር ከተገኘ እናቆምና አዲሱን ዋጋ እናሳይዎታለን፤ እርስዎ ካልፈቀዱ አንቀጥልም።
መሣሪያዎቹ የተጸዱ መሆናቸውን እንዴት አውቃለሁ?
እያንዳንዱ ስብስብ በታሸገ ከረጢት ውስጥ ሆኖ ከፊትዎ ይከፈታል። ከረጢቱ ላይ ያለው ጠቋሚ ቀለሙን ካልቀየረ አውቶክሌቭ አላለፈም ማለት ነው — እንዲያዩት እንፈልጋለን።
ማታ ላይ ጥርሴ ቢያመኝ?
ለ8890 ይደውሉ። እስከ 22:00 ድረስ ይነሳል፤ ካልተነሳ በቴሌግራም ይጻፉልን። አብዛኛው የሌሊት ሕመም እስከ ጠዋት በሕመም ማስታገሻ ይቆያል፣ የፊት እብጠት ግን ወዲያውኑ መታየት አለበት።
ልጅን ከስንት ዓመት ጀምሮ ማምጣት አለብኝ?
የመጀመሪያው ጥርስ ከወጣ በኋላ ወይም በአንድ ዓመቷ። የመጀመሪያዎቹ ጉብኝቶች መቁጠር እና ማሳየት ብቻ ናቸው — ምንም ሥራ አንሠራም።
መኪና የት አቆማለሁ?
በሕንጻው ጓሮ ስምንት ቦታ አለ። ከሞላ ከዓለም ባንክ በተቃራኒ በኩል ያለው መንገድ ላይ ማቆም ይችላሉ።
የሚያመውን ጥርስ ፎቶ ይላኩ
ፎቶውን እና ሕመሙ የጀመረበትን ቀን ይላኩ — ድንገተኛ መሆኑን ወይም እስከ ቀጠሮዎ መጠበቅ እንደሚችል እንነግርዎታለን።