የመግቢያ እና መውጫ ሰዓት
- ሰኞ–ሐሙስ
- 07:30 – 17:30
- ዓርብ
- 07:30 – 16:00
- ቅዳሜ
- ጉብኝት በቀጠሮ ብቻ
- እሁድ
- ዝግ
ከ17:30 በኋላ ለሚዘገዩ በየ15 ደቂቃው 50 ብር ይታሰባል።
+251 11 667 2140ወላጆች የሚጠይቁት
ልጄ ሲለቀቅ ካለቀሰስ?
የመልመጃ ሳምንት አለን — በመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ልጅዎ ለሁለት ሰዓት ብቻ ይቆያል፣ እርስዎም አብረው ሊቆዩ ይችላሉ። አብዛኞቹ ልጆች በሁለተኛው ሳምንት ይለምዳሉ።
ልጅ ቢታመም ምን ታደርጋላችሁ?
ወዲያውኑ እንደውልልዎታለን። ትኩሳት ካለ በተለየ ክፍል ውስጥ ከነርስ ጋር ይቆያል። መድኃኒት የምንሰጠው በጽሑፍ ፈቃድ ብቻ ነው።
ልጁን ማን ሊወስድ ይችላል?
በምዝገባ ወቅት እስከ ሦስት ሰዎችን ከፎቶ ጋር ይመዘግባሉ። ከዝርዝሩ ውጪ ላለ ሰው በቴሌግራም ማረጋገጫ እንጠይቃለን።
በምን ቋንቋ ታስተምራላችሁ?
ጠዋት በአማርኛ፣ ከሰዓት በእንግሊዝኛ። መሸጋገሪያ ክፍል ሁለቱንም ፊደላት ይማራል።
ቦታ አለ?
መስከረም ላይ ሁሉም ክፍሎች ይሞላሉ። በጥር እና በሚያዝያ የሚለቀቅ ቦታ ስላለ ስምዎን በዝርዝሩ ላይ ያስቀምጡ።
ጉብኝት በቴሌግራም ይያዙ
የልጅዎን ዕድሜ እና የሚመችዎትን ቀን ይላኩ — ጉብኝቱ 30 ደቂቃ ነው፣ ልጅዎን ይዘው ይምጡ።