ቧንቧ ወይም መብራት ቢበላሽ ማን ይጠግናል?
የሕንጻው ወይም የመሠረተ ልማት ጥገና የአከራዩ ነው — በቴሌግራም ቢያሳውቁን በ48 ሰዓት ውስጥ ባለሙያ እንልካለን። በተከራዩ ቸልተኝነት የደረሰ ጉዳት ግን በተከራዩ ይሸፈናል።
ኪራዩ በዓመቱ ውስጥ ሊጨምር ይችላል?
አይችልም። በውሉ ጊዜ ውስጥ ኪራዩ ቋሚ ነው። ውሉ ሲታደስ ለውጥ ካለ ከሁለት ወር በፊት በጽሑፍ ይነገርዎታል።
አከራይ ነኝ፤ ንብረቴን ማስተዳደር ትችላላችሁ?
እንችላለን። ተከራይ እንፈልጋለን፣ ኪራዩን በየሦስት ወሩ ሰብስበን ወደ ሒሳብዎ እናስተላልፋለን፣ ጥገናውንም እናስተባብራለን። ክፍያው ከወርሃዊ ኪራዩ 7% ነው።
ኪራይ ጥያቄ በቴሌግራም
የሚፈልጉትን ንብረት፣ ቀን እና ስልክ ይላኩ።