የዚህ ሳምንት ምናሌ
ገበያው የሚወስነው ምናሌ
ሁሉም ዋጋ በብር ነው። በሳምንት አራት ጊዜ ከሾላ እና ከአትክልት ተራ የምንገዛው ምርት ሳህኖቻችንን ይለውጣል።
ጠረጴዛ ያስይዙየግል ጠረጴዛ ጥቅሎች
ዋጋዎቹ በአንድ ሰው ናቸው፤ አገልግሎትና ግብር ተካትቷል።
የአምስት ሳህን ቅምሻ
1950 ብርበአንድ ሰው
ለጥንዶች እና ለአነስተኛ ጠረጴዛዎች
- አምስት ሳህን ከዚህ ሳምንት ገበያ
- የጾም አማራጭ ያለ ተጨማሪ ክፍያ
- ከኤስፕረሶ ጋር መጨረሻ
የሼፍ ጠረጴዛ
2850 ብርበአንድ ሰው · ስድስት መቀመጫ
ከኩሽናው ፊት ለፊት — ሼፉ እያንዳንዱን ሳህን እያስረዳ ያቀርባል
- ሰባት ሳህን የቅምሻ ምናሌ
- ከወይን ወይም ከጭማቂ ጋር ጥምረት
- ከምግብ በኋላ የኩሽና ጉብኝት
- ከሶስት ቀን በፊት ማስያዝ
ሙሉ ቤት ኪራይ
በጥያቄ
- አዳራሹና በረንዳው ለእርስዎ ብቻ
- ከዋና ሼፍ ጋር የተዘጋጀ ምናሌ
- ከሁለት ሳምንት በፊት ማሳወቅ
ማንኛውም ጥቅል የጾም አማራጭ አለው — ሲያስይዙ ብቻ ይንገሩን።
ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
ጠረጴዛ ማስያዝ አለብኝ?
በሳምንቱ ቀናት ቀጥታ መምጣት ይችላሉ። ዓርብ እና ቅዳሜ ግን ሃያ ስምንት መቀመጫ ብቻ ስላለን አስቀድመው ያስይዙ።
የጾም እና የአትክልት ምግብ አላችሁ?
አዎ። የወቅቱ አትክልት ሳህን ሙሉ በሙሉ የጾም ነው፣ ሪዞቶውና ሸርቤቱም ያለ ወተት ይዘጋጃሉ። በጾም ወራት ተጨማሪ ሁለት ሳህን እንጨምራለን።
መኪና የት አቆማለሁ?
ከህንጻው ጀርባ ስምንት የመኪና ማቆሚያ አለን፤ ሲሞላ ጠባቂው በአትላስ መንገድ ላይ ያሳይዎታል።
ለቢሮ ወይም ለልደት ሙሉ ቤቱን መከራየት ይቻላል?
ይቻላል — እስከ 40 እንግዳ። ከሁለት ሳምንት በፊት ያሳውቁን፤ ምናሌውን ከዋና ሼፍ ጋር አብረን እናዘጋጃለን።
በቴሌግራም ይዘዙ
ጠረጴዛ ወይም ለመውሰድ — በፍጥነት እንመልሳለን።