ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
ለመከራየት ምን ማቅረብ አለብኝ?
ትክክለኛ የመንጃ ፈቃድ፣ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት፣ እና ተመላሽ የሚደረግ ተቀማጭ ገንዘብ። ዕድሜ ከ22 ዓመት በላይ።
የኪሎ ሜትር ገደብ አለው?
በቀን 200 ኪሎ ሜትር ተካትቷል፤ ከዚያ በላይ በኪሎ ሜትር 15 ብር ይታሰባል። ወርሃዊ ኪራይ 4,000 ኪ.ሜ ያካትታል።
ነዳጅ ማን ይሸፍናል?
መኪናው ሙሉ ታንክ ይሰጣል፤ ሙሉ ሆኖ መመለስ አለበት። ያልተሞላ ከሆነ የነዳጁ ዋጋ ከተቀማጩ ይቀነሳል።
አሽከርካሪ ማግኘት ይቻላል?
ይቻላል — በቀን 800 ብር ተጨማሪ። ለክልል ጉዞና ለኮስተር አሽከርካሪ የግድ ነው።
መኪና ያስይዙ
ቀን፣ ሞዴል እና የመውሰጃ ቦታ ይላኩልን።